አጭር ዓላማ መግለጫ
ጎዳና የብዙኀን መገናኛ አውድ ቢሆንም፥ አንድ ቡድን ከስክሪን ጀርባ ሆኖ ከስክሪን ወዲያ ላለ ‘ሕዝብ’ ይገባዋል ያለውን ይዘት የሚያቀርብበት መደብ - አይደለም። ይልቁንም - እንደ አንድ ነጻ ጎዳና - አላፊ አግዳሚው ይበጃልም ይበጀኛልም የሚለውን ጉዳይ ለኩሶ፥ ውይይት የመጀመር ግብ ብቻ ያነገበ ነው። “ሀገራችን ሰፊ - ጎዳናውም ብዙ ሆኖ ሳለ- ለምን ብለን ለጎዳና ጨዋታ በይነ መረብ ላይ?” የሚል ጥያቄ መነሳቱ አይቀርም ብለን “እኛም ጠርጥረናል”። ያገሬው ሰው ጎዳናው ጆሮ ይኖረው ይሆን ብሎ ሰግቶ፤ ሰምቶም ለባለወንበር ያሳበቀስ እንደሁ ሲል ጠርጥሮ ዝም ማለቱን ተመልክተን፥ እነሆ በጎ ፈቃደኛ ሰዎች ጎዳናን “አንጻራዊ ሰላም” ወዳለው ቦታ ይዘን መጥተናል። እንደማንኛውም አላፊ አግዳሚ እኛም ሲጠይቁን “ፖለቲካ አንወድም” እንላለን - ስለዚህም “ገብስ ገብሱን”። የአገራችን ጎዳና ከጥይት እና ፍርድ ግምደላ የተረፈ እንደሆነ - ይህ - የእናንተ - የእኛ - ጎዳና ብዕራችሁን ወደ መሬት ይመልሳል። እስከዛ ግን ውይይት እየጠነሰስን መድረኩን ለእናንተ መንገደኞች እንከፍታለን። ማንኛውንም ውይይት ግን እንቋጫለን ብለን ቃል - አ∙ን∙ገ∙ባ∙ም - ቁጭቱን መንገደኛው በየቤቱ። ሙሉ ይዘቶች በቅርብ ቀን